Loading...
Language: Amharic
وَإِذْ صَرَفْنَا إِلَيْكَ نَفَرًا مِّنَ الْجِنِّ يَسْتَمِعُونَ الْقُرْآنَ فَلَمَّا حَضَرُوهُ قَالُوا أَنصِتُوا ۖ فَلَمَّا قُضِيَ وَلَّوْا إِلَىٰ قَوْمِهِم مُّنذِرِينَ ﴿٢٩﴾ قَالُوا يَا قَوْمَنَا إِنَّا سَمِعْنَا كِتَابًا أُنزِلَ مِن بَعْدِ مُوسَىٰ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ يَهْدِي إِلَى الْحَقِّ وَإِلَىٰ طَرِيقٍ مُّسْتَقِيمٍ ﴿٣٠﴾ يَا قَوْمَنَا أَجِيبُوا دَاعِيَ اللَّـهِ وَآمِنُوا بِهِ يَغْفِرْ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمْ وَيُجِرْكُم مِّنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ ﴿٣١﴾ وَمَن لَّا يُجِبْ دَاعِيَ اللَّـهِ فَلَيْسَ بِمُعْجِزٍ فِي الْأَرْضِ وَلَيْسَ لَهُ مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءُ ۚ أُولَـٰئِكَ فِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ ﴿٣٢﴾
ወኢዝ ሰረፍና ኢለይከ ነፈረም ሚነል ጂኒ የስተሚዑነል ቁርአነ ፈለማ ሀደሩሁ ቃሉ አንሲጡ ፈለማ ቁዲየ ወለው ኢላ ቀውሚሂም ሙንዚሪን። ቃሉ ያ ቀውመና ኢንና ሰሚዕና ኪታበን ኡንዚለ ሚም ባዕዲ ሙሳ ሙሰዲቀል ሊማ በይነ የደይሂ የህዲ ኢለል ሀቁ ወኢላ ጠሪቂም ሙስተቂም። ያ ቀውመና አጂቡ ዳዒየላሂ ወአሚኑ ቢሂ የግፊር ለኩም ሚን ዙኑቢኩም ወዩጂርኩም ሚን ዐዛቢን አሊም። ወመላ ዩጂብ ዳዒየላሂ ፈለይሰ ቢሙዕጂዚን ፊል አርዲ ወለይሰ ለሁ ሚን ዱኒሂ አውሊያእ፤ ኡላኢከ ፊ ዶላሊም ሙቢን።
(29) ከጂኖችም ጭፍሮችን ቁርአንን የሚያዳምጡ ሆነው ወደ አንተ ባዞርን ጊዜ (አስታውስ)፤ በተገኙበትም ጊዜ «ዝም ብላችሁ ስሙ» ተባባሉ፤ (ንባቡ) በተጨረሰም ጊዜ ወደ ወገኖቻቸው አስጠንቃቂዎች ሆነው ተመለሱ። (30) «ወገኖቻችን ሆይ! እኛ ከሙሳ በኋላ የተወረደን፣ በፊቱ ያለውን የሚያረጋግጥን፣ ወደ እውነትና ወደ ቀጥተኛው መንገድ የሚመራን መጽሐፍ ሰማን» አሉ። (31) «ወገኖቻችን ሆይ! የአላህን ተጣሪ ተቀበሉ፤ በርሱም እመኑ፤ ከኃጢአቶቻችሁ ለናንተ ይምርላችኋልና፤ ከአሳማሚ ቅጣትም ያድናችኋልና።» (32) «የአላህንም ተጣሪ የማይቀበል ሰው በምድር ላይ (አላህን) የሚያመልጥ አይደለም፤ ከርሱም ሌላ ረዳቶች የሉትም፤ እነዚያ በግልጽ ስህተት ውስጥ ናቸው።» (ሱረቱ አል-አህቃፍ፡ 29-32)
Reference: ሱራ አል-አህቃፍ ፵፮: ፳፱-፴፪