Loading...
Language: Amharic
لَوْ أَنزَلْنَا هَـٰذَا الْقُرْآنَ عَلَىٰ جَبَلٍ لَّرَأَيْتَهُ خَاشِعًا مُّتَصَدِّعًا مِّنْ خَشْيَةِ اللَّـهِ ۚ وَتِلْكَ الْأَمْثَالُ نَضْرِبُهَا لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ ﴿٢١﴾ هُوَ اللَّـهُ الَّذِي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ ۖ هُوَ الرَّحْمَـٰنُ الرَّحِيمُ ﴿٢٢﴾ هُوَ اللَّـهُ الَّذِي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ ۚ سُبْحَانَ اللَّـهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ ﴿٢٣﴾ هُوَ اللَّـهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ۚ يُسَبِّحُ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ ﴿٢٤﴾
ለው አንዘልና ሀዘል ቁርአነ ዐላ ጀበሊል ለረአይተሁ ኻሺዐም ሙተሰዲዐም ሚን ኸሽየቲላህ፤ ወቲልከል አምሳሉ ነድሪቡሀ ሊናሲ ለዐለሁም የተፈከሩን። ሁወላሁለዚ ላ ኢላሀ ኢላ ሁወ ዐሊሙል ገይቢ ወሸሀደህ፤ ሁወር ረህማኑር ረሂም። ሁወላሁለዚ ላ ኢላሀ ኢላ ሁወል መሊኩን ቁዱሱ ሰላሙል ሙእሚኑል ሙሀይሚኑል ዐዚዙል ጀባሩል ሙተከቢር፤ ሱብሀነላሂ ዐማ ዩሽሪኩን። ሁወላሁል ኻሊቁል ባሪኡል ሙሰዊሩ ለሁል አስማኡል ሁስና፤ ዩሰቢሁ ለሁ ማ ፊስ ሰማዋቲ ወል አርድ፤ ወሁወል ዐዚዙል ሀኪም።
(21) ይህን ቁርአን በተራራ ላይ ባወረድነው ኖሮ፣ ከአላህ ፍራቻ የተነሳ ተዋራጅና ተሰንጣቂ ሆኖ ባየኸው ነበር፤ እነዚህም ምሳሌዎች ያስተውሉ ዘንድ ለሰዎች እንገልጻቸዋለን። (22) እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ሩቁንም ቅርቡንም አዋቂ ነው፤ እርሱ እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ ነው። (23) እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሱ፣ ከጉድለት የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ፣ ጸጥታን ሰጪው፣ ባሮቹን ጠባቂው፣ አሸናፊው፣ ኃያሉ፣ ኩሩው ነው፤ አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ። (24) እርሱ አላህ ፈጣሪው፣ (ከለለሞት) አስገኚው፣ ቅርጽን አውጪው ነው፤ ለርሱ መልካም ስሞች አሉት፤ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ለርሱ ያሞግሳል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው። (ሱረቱ አል-ሀሽር፡ 21-24)
Reference: ሱራ አል-ሐሽር ፶፱: ፳፩-፳፬