Loading...
Language: Amharic
بِسْمِ اللَّـهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ قُلْ أُوحِيَ إِلَيَّ أَنَّهُ اسْتَمَعَ نَفَرٌ مِّنَ الْجِنِّ فَقَالُوا إِنَّا سَمِعْنَا قُرْآنًا عَجَبًا ﴿١﴾ يَهْدِي إِلَى الرُّشْدِ فَآمَنَّا بِهِ ۖ وَلَن نُّشْرِكَ بِرَبِّنَا أَحَدًا ﴿٢﴾ وَأَنَّهُ تَعَالَىٰ جَدُّ رَبِّنَا مَا اتَّخَذَ صَاحِبَةً وَلَا وَلَدًا ﴿٣﴾ وَأَنَّهُ كَانَ يَقُولُ سَفِيهُنَا عَلَى اللَّـهِ شَطَطًا ﴿٤﴾ وَأَنَّا ظَنَنَّا أَن لَّن تَقُولَ الْإِنسُ وَالْجِنُّ عَلَى اللَّـهِ كَذِبًا ﴿٥﴾ وَأَنَّهُ كَانَ رِجَالٌ مِّنَ الْإِنسِ يَعُوذُونَ بِرِجَالٍ مِّنَ الْجِنِّ فَزَادُوهُمْ رَهَقًا ﴿٦﴾ وَأَنَّهُمْ ظَنُّوا كَمَا ظَنَنتُمْ أَن لَّن يَبْعَثَ اللَّـهُ أَحَدًا ﴿٧﴾ وَأَنَّا لَمَسْنَا السَّمَاءَ فَوَجَدْنَاهَا مُلِئَتْ حَرَسًا شَدِيدًا وَشُهُبًا ﴿٨﴾ وَأَنَّا كُنَّا نَقْعُدُ مِنْهَا مَقَاعِدَ لِلسَّمْعِ ۖ فَمَن يَسْتَمِعِ الْآنَ يَجِدْ لَهُ شِهَابًا رَّصَدًا ﴿٩﴾
ቢስሚላሂር ረህማኒር ረሂም። ቁል ኡሂየ ኢለይየ አንነሁስተመዐ ነፈሩም ሚነል ጂኒ ፈቃሉ ኢንና ሰሚዕና ቁርአነን ዐጀባ። የህዲ ኢለር ሩሽዲ ፈአመና ቢሂ ወለን ኑሽሪከ ቢረቢና አሀዳ። ወአንነሁ ተዐላ ጀዱ ረቢና መተኸዘ ሳሂበተን ወላ ወለዳ። ወአንነሁ ካነ የቁሉ ሰፊሁና ዐለላሂ ሸጠጣ። ወአንና ዘነና አለን ተቁለል ኢንሱ ወል ጂኑ ዐለላሂ ከዚባ። ወአንነሁ ካነ ሪጃሉም ሚነል ኢንሲ የዑዙነ ቢሪጃሊም ሚነል ጂኒ ፈዛዱሁም ረሀቃ። ወአንነሁም ዘኑ ከማ ዘነንቱም አለን የብዐሰላሁ አሀዳ። ወአንና ለመስነስ ሰማአ ፈወጀድናሀ ሙሊአት ሀረሰን ሸዲደን ወሹሁባ። ወአንና ኩና ነቅዑዱ ሚንሀ መቃዒደ ሊሰምዒ ፈመን የስተሚዒል አነ የጂድ ለሁ ሺሀበን ረሰዳ።
(1) በል፡- «ከጂን የሆነ ጭፍራ (ቁርአንን) አዳመጡ፤ እንዲህም አሉ ማለት ወደኔ ተወረደ፡- እኛ አስደናቂ የሆነን ቁርአን ሰማን። (2) ወደ ቅን መንገድ የሚመራን (ቁርአን ሰማን)፤ በርሱም አመንን፤ በጌታችንም አንድንም አናጋራም። (3) የጌታችንም ጌትነት ላቀ፤ ሚስትንም ልጅንም አልያዘም። (4) እኛ ሞኛችንም በአላህ ላይ ከአውነት የራቀን ውሸት ይናገር ነበር። (5) እኛም ሰዎችና ጂኖች በአላህ ላይ ውሸትን አይናገሩም ብለን ጠረጠर्न። (6) ከሰዎችም የሆኑ ወንዶች ከጂን በሆኑ ወንዶች ይጠበቁ ነበር (በዚህም) ኩራትን ጨመሩላቸው። (7) እነሱም እንደ ጠረጠራችሁት አላህ አንድንም አይልክም ብለው ጠረጠሩ። (8) እኛም ሰማይን ፈለግን፤ ኃይለኞችን ጠባቂዎችና የእሳት ራት (ከዋክብት) ተሞልታ አገኘናት። (9) እኛም ከርሷ ለመስማት መቀመጫዎች ላይ እንቀመጥ ነበር፤ አሁን ግን የሚያዳምጥ ሰው ለርሱ የሚጠባበቅን የእሳት ራት ያገኛል። (ሱረቱ አል-ጂን፡ 1-9)
Reference: ሱራ አል-ጂን ፸፪: ፩-፱