Loading...
Language: Amharic
إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا وَصَدُّوا عَن سَبِيلِ اللَّـهِ قَدْ ضَلُّوا ضَلَالًا بَعِيدًا ﴿١٦٧﴾ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا وَظَلَمُوا لَمْ يَكُنِ اللَّـهُ لِيَغْفِرَ لَهُمْ وَلَا لِيَهْدِيَهُمْ طَرِيقًا ﴿١٦٨﴾ إِلَّا طَرِيقَ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّـهِ يَسِيرًا ﴿١٦٩﴾ يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمُ الرَّسُولُ بِالْحَقِّ مِن رَّبِّكُمْ فَآمِنُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ وَإِن تَكْفُرُوا فَإِنَّ لِلَّـهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَكَانَ اللَّـهُ عَلِيمًا حَكِيمًا ﴿١٧٠﴾ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا عَلَى اللَّـهِ إِلَّا الْحَقَّ ۚ إِنَّمَا الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ اللَّـهِ وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِّنْهُ ۖ فَآمِنُوا بِاللَّـهِ وَرُسُلِهِ ۖ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّـهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ سُبْحَانَهُ أَن يَكُونَ لَهُ وَلَدٌ ۘ لَّهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِاللَّـهِ وَكِيلًا ﴿١٧١﴾ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّـهِ وَلَا الْمَلَائِكَةُ الْمُقَرَّبُونَ ۚ وَمَن يَسْتَنكِفْ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيَسْتَكْبِرْ فَسَيَحْشُرُهُمْ إِلَيْهِ جَمِيعًا ﴿١٧٢﴾ فَأَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فَيُوَفِّيهِمْ أُجُورَهُمْ وَيَزِيدُهُم مِّن فَضْلِهِ ۖ وَأَمَّا الَّذِينَ اسْتَنكَفُوا وَاسْتَكْبَرُوا فَيُعَذِّبُهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا وَلَا يَجِدُونَ لَهُم مِّن دُونِ اللَّـهِ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا ﴿١٧٣﴾
ኢንነለዚነ ከፈሩ ወሰዱ ዐን ሰቢሊላሂ ቀድ ዶሉ ዶላለም በዒዳ። ኢንነለዚነ ከፈሩ ወዘለሙ ለም የኩኒላሁ ሊየግፊረ ለሁም ወላ ሊየህዲየሁም ጠሪቃ። ኢላ ጠሪቀ ጀሀነመ ኻሊዲነ ፊሀ አበዳ፤ ወካነ ዛሊከ ዐለላሂ የሲራ። ያ አዩሀን ናሱ ቀድ ጃአኩሙር ረሱሉ ቢልሀቂ ሚር ረቢኩም ፈአሚኑ ኸይረል ለኩም፤ ወኢን ተክፉሩ ፈኢንነ ሊላሂ ማ ፊስ ሰማዋቲ ወል አርድ፤ ወካነላሁ ዐሊመን ሀኪማ። ያ አህለል ኪታቢ ላ ተግሉ ፊ ዲኒኩም ወላ ተቁሉ ዐለላሂ ኢለል ሀቅ፤ ኢንነመል መሲሁ ዒሰብሊ መርየመ ረሱሉላሂ ወከሊመቱሁ አልቃሀ ኢላ መርየመ ወሩሁም ሚንህ፤ ፈአሚኑ ቢላሂ ወሩሱሊሂ ወላ ተቁሉ ሰላሰህ፤ ኢንተሁ ኸይረል ለኩም፤ ኢንነመላሁ ኢላሁን ዋሂድ፤ ሱብሀነሁ አን የኩነ ለሁ ወለድ፤ ለሁ ማ ፊስ ሰማዋቲ ወማ ፊል አርድ፤ ወከፋ ቢላሂ ወኪላ። ለን የስተንኪፈል መሲሁ አን የኩነ ዐብደል ሊላሂ ወለል መላኢከቱል ሙቀረቡን፤ ወመን የስተንኪፍ ዐን ዒባደቲሂ ወየስተክቢር ፈሰየህሹሩሁም ኢለይሂ ጀሚዐ። ፈአመለዚነ አመኑ ወዐሚሉስ ሷሊሀቲ ፈዩወፊሂም ኡጁረሁም ወየዚዱሁም ሚን ፈድሊህ፤ ወአመለዚነስ ተንከፉ ወስተክበሩ ፈዩዐዚቡሁም ዐዛበን አሊመን ወላ የጂዱነ ለሁም ሚን ዱኒላሂ ወሊየን ወላ ነሲራ።
(167) እነዚያ የካዱ ከአላህ መንገድም የከለከሉ (ሰዎች)፣ በእርግጥ የራቀን መሳሳት ሳቱ። (168) እነዚያ የካዱ፣ የበደሉም፣ አላህ ለነርሱ ሊምርላቸው፤ መንገድንም ሊመራቸው አይደለም። (169) የገሀነምን መንገድ ብቻ ሲቀሩ፤ በውስጧ ዘላለም የሚዘውትሩ ሲሆኑ (ይቀጣቸዋል)፤ ይህም በአላህ ላይ ቀላል ነው። (170) እናንተ ሰዎች ሆይ! መልእክተኛው ከጌታችሁ በሆነ እውነት በእርግጥ መጣላችሁ፤ እመኑም፤ ለናንተ የተሻለ ነውና፤ ብትክዱም፣ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ለአላህ ነው (አትጎዱትም)፤ አላህም አዋቂ ጥበበኛ ነው። (171) እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ፤ አልመሲህ ዒሳ የማርያም ልጅ የአላህ መልእክተኛ፣ ወደ ማርያምም የጣላት ቃሉ፣ ከርሱም የሆነ መንፈስ ብቻ ነው፤ በአላህና በመልእክተኞቹም እመኑ፤ (አማልክት) ሶስት ናቸው አትበሉም፤ ተከልከሉ፤ ለናንተ የተሻለ ይሆናልና፤ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ለርሱ ልጅ ያለው ከመሆን ጥራት ይገባው፤ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ነው፤ መካያም በአላህ በቃ። (172) አልመሲህ ለአላህ ባሪያ ከመሆን ፈጽሞ አይጠየፍም፤ ቀራቢዎች መላእክትም (አይጠየፉም)፤ እርሱን ከመገዛት የሚጠየፍና የሚኮራም ሰው፣ (አላህ) ሁሉንም ወደርሱ ይሰበስባቸዋል። (173) እነዚያማ ያመኑትና መልካም ስራዎችን የሰሩት፣ ምንዳዎቻቸውን ይሞላላቸዋል፤ ከትሩፋቱም ይጨምርላቸዋል፤ እነዚያን የተጠየፉትንና የኮሩትን ግን አሳማሚን ቅጣት ይቀጣቸዋል፤ ከአላህም ሌላ ለነርሱ ዘመድንና ረዳትን አያገኙም። (ሱረቱ አን-ኒሳእ፡ 167-173)
Reference: ሱራ አን-ኒሳእ ፬: ፻፷፯-፻፸፫