Loading...
Language: Amharic
የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) አንድ ሰው ሲል ሰሙት -
اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ بِأَنِّي أَشْهَدُ أَنَّكَ اَنْتَ اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ الْأَحَدُ الصَّمَدُ الَّذِيْ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُوْلَدْ وَلَمْ يَكُنْ لَهُ كُفُوًا أَحَدٌ
አላሁመ ኢኒ አሰአሉከ ቢ አኒ አሽ-ሀዱ አነከ አንተላሁ ላ ኢላሀ ኢላ አንተል-አሀዱስ-ሰመዱል-ለዚ ለም የሊድ ወ ለም ዩለድ ወ ለም የኩን ለሁ ኩፉወን አሀድ
አላህ ሆይ፣ እኔ፣ አንተ አላህ እንደሆንክ በመመስከር እጠይቅሃለሁ። ከአንተ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ አንተ ብቸኛ አምላክ ነህ፣ ከፍጡራን የተብቃቃህ፣ ያልወለደ እና ያልተወለደ፣ እና ለእርሱም ማንም እኩያ የሌለው። የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- «ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ፣ አላህን በታላቁ ስሙ ጠርቶታል፤ በዚህ (ስም) በተጠራ ጊዜ ይመልሳል፤ በዚህም ሲጠየቅ ይሰጣል።»
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። አቡ ዳውድ፡ ፲፬፻፺፫