Loading...
Language: Amharic
إِنَّمَا جَزَاءُ الَّذِينَ يُحَارِبُونَ اللَّـهَ وَرَسُولَهُ وَيَسْعَوْنَ فِي الْأَرْضِ فَسَادًا أَن يُقَتَّلُوا أَوْ يُصَلَّبُوا أَوْ تُقَطَّعَ أَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُم مِّنْ خِلَافٍ أَوْ يُنفَوْا مِنَ الْأَرْضِ ۚ ذَٰلِكَ لَهُمْ خِزْيٌ فِي الدُّنْيَا ۖ وَلَهُمْ فِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ ﴿٣٣﴾ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا مِن قَبْلِ أَن تَقْدِرُوا عَلَيْهِمْ ۖ فَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّـهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ﴿٣٤﴾
ኢንነማ ጀዛኡለዚነ ዩሀሪቡነላሀ ወረሱለሁ ወየስዐውነ ፊል አርዲ ፈሳደን አን ዩቀተሉ አው ዩሰለቡ አው ቱቀጠዐ አይዲሂም ወአርጁሉሁም ሚን ኺላፊን አው ዩንፈው ሚነል አርድ፤ ዛሊከ ለሁም ኺዝዩን ፊድ ዱንያ ወለሁም ፊል አኺረቲ ዐዛቡን ዐዚም። ኢለለዚነ ታቡ ሚን ቀብሊ አን ተቅዲሩ ዐለይሂም ፈዕለሙ አንነላሀ ገፉሩር ረሂም።
(33) የነዚያ አላህንና መልእክተኛውን የሚዋጉ፣ በምድርም ላይ ለማጥፋት የሚጥሩ ሰዎች ቅጣት፣ መገደል፣ ወይም መሰቀል፣ ወይም እጅና እግሮቻቸውን በማፈራረቅ መቆረጥ፣ ወይም ከአገር መባረር ብቻ ነው፤ ይህ ለነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት ነው፤ ለነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ታላቅ ቅጣት አላቸው። (34) እነዚያ በነሱ ላይ ከመውደቃችሁ (ከመቻላችሁ) በፊት የተጸጸቱ ሲቀሩ፤ አላህም መማር አዛኝ መሆኑን እወቁ። (ሱረቱ አል-ማኢዳህ፡ 33-34)
Reference: ሱራ አል-ማኢዳህ ፭: ፴፫-፴፬