Loading...
Language: Amharic
رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَـٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ ﴿١٩١﴾ رَبَّنَا إِنَّكَ مَن تُدْخِلِ النَّارَ فَقَدْ أَخْزَيْتَهُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ ﴿١٩٢﴾ رَّبَّنَا إِنَّنَا سَمِعْنَا مُنَادِيًا يُنَادِي لِلْإِيمَانِ أَنْ آمِنُوا بِرَبِّكُمْ فَآمَنَّا ۚ رَبَّنَا فَاغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّئَاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ الْأَبْرَارِ ﴿١٩٣﴾ رَبَّنَا وَآتِنَا مَا وَعَدتَّنَا عَلَىٰ رُسُلِكَ وَلَا تُخْزِنَا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ إِنَّكَ لَا تُخْلِفُ الْمِيعَادَ ﴿١٩٤﴾
ረበና ማ ኸለቅተ ሀዛ ባጢለን ሱብሀነከ ፈቂና ዐዛበን ናር። ረበና ኢንነከ መን ቱድኺሊን ናረ ፈቀድ አኽዘይተሁ ወማ ሊዝዞሊሚነ ሚን አንሷር። ረበና ኢንነና ሰሚዕና ሙናዲየን ዩናዲ ሊል ኢማኒ አን አሚኑ ቢረቢኩም ፈአመና፤ ረበና ፈግፊር ለና ዙኑገና ወከፊር ዐንና ሰይይአቲና ወተወፈና መዐል አብራር። ረበና ወአቲና ማ ወዐድተና ዐላ ሩሱሊከ ወላ ቱኽዚና የውመል ቂያመህ፤ ኢንነከ ላ ቱኽሊፉል ሚዒአድ።
ጌታችን ሆይ! ይህንን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቀን። (191) ጌታችን ሆይ! አንተ በእሳት የምታስገባውን ሰው በእርግጥ አዋረድከው፤ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም። (192) ጌታችን ሆይ! እኛ ወደ እምነት «በጌታችሁ እመኑ» በማለት የሚጠራን ጠሪ ሰማን፤ አመንንም። ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንን ለኛ ማርልን፤ ክፉ ስራዎቻችንንም ከኛ አብስልን፤ ከመልካሞቹም ሰዎች ጋር ግደለን። (193) ጌታችን ሆይ! በመልክተኞችህም ላይ ቃል የገባህልንን ስጠን፤ በትንሳኤ ቀንም አታዋርደን፤ አንተ ቀጠሮን አታፈርስምና። (194) (ሱረቱ አሊ-ዒምራን፡ 191-194)
Reference: ሱራ አሊ ኢምራን ፫:፻፺፩-፻፺፬