Loading...
Language: Amharic
ኢብን አባስ (ረ.ዐ) እንደዘገቡት፡- ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «በሌሎች ቀናት የሚሰሩ መልካም ስራዎች በእነዚህ ቀናት (በመጀመሪያዎቹ አስር የዙል ሂጃ ቀናት) ከተሰሩት አይበልጡም።» ከዚያም አንዳንድ የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ባልደረቦች፡- «ጂሃድም ቢሆን?» አሉ። እሳቸውም መለሱ፡- «ጂሃድም ቢሆን፤ አንድ ሰው ነፍሱን እና ንብረቱን ለአደጋ አጋልጦ (ለአላህ ብሎ) ወጥቶ ከነዚያ ነገሮች በምንም ሳይመለስ የቀረ ሰው እንጂ።»
Reference: ቡኻሪ፡ ፱፻፷፱