Loading...
Language: Amharic
ከኡሙ ደርዳእ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው፣ ለሶፍዋን (ረ.ዐ) እንዲህ አለችው፡- በዚህ አመት ሀጅ የማድረግ ሀሳብ አለህ? እኔም፡- አዎ አልኩ። እርሷም አለች፡- የአላህን በረከት በላያችን እንድናገኝ ዱዓ አድርግልን፤ ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ይሉ ነበርና፡- አንድ ሙስሊም ለወንድሙ በሌለበት የሚያደርገው ዱዓ ተቀባይነት አለው፤ ለወንድሙ በረከትን በጠየቀ ቁጥር የተመደበው መልአክ፡- አሜን፣ ለአንተም እንዲሁ ይሁንልህ ይላል።
Reference: ሙስሊም፡ ፳፯፻፴፫