Loading...
Language: Amharic
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ዱዓቸው የማይመለስባቸው ሶስት ሰዎች አሉ፡- ጾመኛ ሲያፈጥር፣ ፍትሃዊ መሪ፣ እና የተበደለ ሰው ዱዓ፤ አላህ (ዱዓውን) ከደመናዎች በላይ ከፍ ያደርገዋል፣ የሰማይ በሮችም ይከፈቱለታል። ጌታም እንዲህ ይላል፡- “በክብሬ እምላለሁ፣ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ቢሆን በእርግጥ እረዳሃለሁ።”»
Reference: ሐሰን። ቲርሚዚ፡ ፴፭፻፺፰