Loading...
Language: Amharic
ዱዓ ተቀባይነት እንዲኖረው ከሚያደርጉ ጠንካራ ምክንያቶች አንዱ በችግር ጊዜ ዱዓ ማድረግ ነው። ለዚህ ማረጋገጫው ስለ ሶስቱ ሰዎች የሚናገረው ሀዲስ ነው፤ በሌሊት በአንድ ዋሻ ውስጥ ለመጠለል ተገደው ነበር። በኋላም ከኮረብታው ላይ ድንጋይ ወድቆ የዋሻውን አፍ ዘጋው። ከዚያም እርስ በርስ እንዲህ ተባባሉ፡- «ለአላህ ብቻ ብላችሁ የሰራችሁትን ስራ ፈልጉ፣ ከዚያም በእነዚያ ስራዎች እርዳታ አላህን ለምኑ፣ ከዚያም ከዚህ እንደሚያወጣችሁ ተስፋ ይደረጋል።» ከዚያም በመልካም ስራቸው ወደ አላህ ጸለዩ። በዚህም ምክንያት ድንጋዩ ተንቀሳቀሰ እና እነርሱም ወጡ።
Reference: ቡኻሪ፡ ፳፪፻፲፭