Loading...
Language: Amharic
اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ مِنَ الْخَيْرِ كُلِّهِ عَاجِلِهِ وَآجِلِهِ مَا عَلِمْتُ مِنْهُ وَمَا لَمْ أَعْلَمْ وَأَعُوْذُ بِكَ مِنَ الشَّرِّ كُلِّهِ عَاجِلِهِ وَآجِلِهِ مَا عَلِمْتُ مِنْهُ وَمَا لَمْ أَعْلَمْ اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ مِنْ خَيْرِ مَا سَأَلَكَ عَبْدُكَ وَنَبِيُّكَ وَأَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا عَاذَ بِهِ عَبْدُكَ وَنَبِيُّكَ اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْجَنَّةَ وَمَا قَرَّبَ إِلَيْهَا مِنْ قَوْلٍ أَوْ عَمَلٍ وَأَعُوْذُ بِكَ مِنَ النَّارِ وَمَا قَرَّبَ إِلَيْهَا مِنْ قَوْلٍ أَوْ عَمَلٍ وَأَسْأَلُكَ أَنْ تَجْعَلَ كُلَّ قَضَاءٍ قَضَيْتَهُ لِي خَيْرًا
አልላሁምመ ኢንኒ አሰአሉከ ሚነል ኸይሪ ኩልሊሂ አጂሊሂ ወአጂሊሂ፣ ማ አሊምቱ ሚንሁ ወማ ለም አእለም፣ ወአዑዙ ቢከ ሚነሽ ሸርሪ ኩልሊሂ አጂሊሂ ወአጂሊሂ፣ ማ አሊምቱ ሚንሁ ወማ ለም አእለም፣ አልላሁምመ ኢንኒ አሰአሉከ ሚን ኸይሪ ማ ሰአለከ አብዱከ ወነቢይዩከ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚን ሸርሪ መስተአዘ ቢሂ አብዱከ ወነቢይዩከ፣ አልላሁምመ ኢንኒ አሰአሉከል ጀንነተ ወማ ቀርረበ ኢለይሀ ሚን ቀውሊን አው አመለ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚነን ናሪ ወማ ቀርረበ ኢለይሀ ሚን ቀውሊን አው አመለ፣ ወአሰአሉከ አን ተጅአለ ኩልለ ቀዷኢን ቀደይተሁ ሊ ኸይራ
«አላህ ሆይ! እኔ መልካም ነገሮችን በሙሉ፣ የቅርቡንም (የአሁኑን) የሩቁንም (የወደፊቱን)፣ ያወቅኩትንም ያላወቅኩትንም እጠይቅሃለሁ። ከክፉ ነገር በሙሉ፣ ከቅርቡም ከሩቁም፣ ካወቅኩትም ካላወቅኩትም በአንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! እኔ ባሪያህ እና ነቢይህ (ሙሐመድ) የጠየቁህን መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ። ባሪያህ እና ነቢይህ ከተጠበቁበት ክፉ ነገር በአንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! እኔ ጀነትን እና ወደርሷ የሚያቀርበውን ንግግር ወይም ስራ እጠይቅሃለሁ። ከእሳት እና ወደርሷ ከሚያቀርበው ንግግር ወይም ስራ ባንተ እጠበቃለሁ። ለእኔ የወሰንከውን ውሳኔ ሁሉ መልካም እንድታደርግልኝም እጠይቅሃለሁ።» (ኢብኑ ማጃህ፡ 3846)
Reference: ሷሒሕ። ኢብን ማጃህ፡ ፫፸፶፮