Loading...
Language: Amharic
የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ይህንን ዱዓ ያደርጉ ነበር፦
اَللَّهُمَّ إِنَّا نَسْأَلُكَ مُوْجِبَاتِ رَحْمَتِكَ وَعَزَائِمَ مَغْفِرَتِكَ وَالسَّلَامَةَ مِنْ كُلِّ إِثْمٍ وَالْغَنِيْمَةَ مِنْ كُلِّ بِرٍّ وَالْفَوْزَ بِالْجَنَّةِ وَالنَّجَاةَ بِعَوْنِكَ مِنَ النَّارِ
አልላሁምመ ኢንና ነስአሉከ ሙጂባቲ ራህመቲከ፣ ወአዛኢመ መግፊረቲከ፣ ወስሰላመተ ሚን ኩልሊ ኢስሚን፣ ወልገኒመተ ሚን ኩልሊ ቢርሪን፣ ወልፈውዘ ቢልጀንነቲ፣ ወንነጃተ ቢአውኒከ ሚነንናር
«አላህ ሆይ! እዝነትህን የሚያስገኙ (ስራዎችን)፣ ምህረትህን የሚያረጋግጡ (ተግባራትን)፣ ከኃጢአት ሁሉ መጠበቅን፣ ከመልካም ነገር ሁሉ መጠቀምን (ምርኮን)፣ በጀነት መደሰትን፣ እና በአንተ እገዛ ከእሳት መትረፍን እንጠይቅሃለን።» (ኢብኑ ማጃህ፡ 3846)
Reference: ሐሰን (አርናኡት)። አል-አዝካር ፩/፫፻፵