Loading...
Language: Amharic
የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) አንድ ሰው ተሸሁድ ላይ ይህንን ዱዓ ሲያደርግ ሰምተው፦ «ተማረለት! ተማረለት! ተማረለት!» በማለት ሶስት ጊዜ መስክረዋል።
اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ يَا اَللَّهُ بِأَنَّكَ الْوَاحِدُ الْأَحَدُ الصَّمَدُ الَّذِي لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ وَلَمْ يَكُنْ لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ أَنْ تَغْفِرَ لِي ذُنُوْبِيْ، إِنَّكَ أَنْتَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከ ያ አላሁ! ቢአንነከል ዋሂዱል አሀዱስ ሰመድ፣ አልለዚ ለም የሊድ ወለም ዩለድ፣ ወለም የኩን ለሁ ኩፉወን አሀድ፣ አን ተግፊረ ሊ ዙኑቢ፣ ኢንነከ አንተል ገፉሩር ረሂም
«አላህ ሆይ! ያ አላህ፣ አንተ አንድ፣ ብቸኛ፣ (ሁሉም ነገር ወደ አንተ) ፈላጊ፣ ያልወለድክ፣ ያልተወለድክ እና አምሳያ የሌለህ በመሆንህ እጠይቅሃለሁ፤ ወንጀሌን ማርልኝ! አንተ መሃሪ እና አዛኝ ነህና።» (አን-ነሳኢ፡ 1301)
Reference: ሷሒሕ። አን-ናሳኢ፡ ፩፫፸፩