Loading...
Language: Amharic
ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) አንድ ሰው ሲጸልይ እንዲህ ሲል ሰሙት -
اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ بِأَنَّ أَشْهَدُ أَنَّكَ أَنْتَ اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ الْأَحَدُ الصَّمَدُ الَّذِيْ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُوْلَدْ وَلَمْ يَكُنْ لَهُ كُفُوًا أَحَدٌ
አላሁመ ኢኒ አሰአሉከ ቢ አኒ አሽ-ሀዱ አነከ አንተላሁ ላ ኢላሀ ኢላ አንተል-አሀዱስ-ሰመዱል-ለዚ ለም የሊድ ወ ለም ዩለድ፣ ወ ለም የኩን ለሁ ኩፉወን አሀድ
አላህ ሆይ፣ እኔ፣ አንተ አላህ እንደሆንክ በመመስከር እጠይቅሃለሁ። ከአንተ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ አንተ ብቸኛ አምላክ ነህ፣ ከፍጡራን የተብቃቃህ፣ ያልወለደ እና ያልተወለደ፣ እና ለእርሱም ማንም እኩያ የሌለው። ከዚያም ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- «አላህን በታላቁ ስሙ ተማጽነሃል፤ በዚህ ስም በተጠየቀ ጊዜ ይሰጣል፤ በዚህ ስም በተጠራ ጊዜ ይመልሳል።»
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። ነሳኢ፡ ፲፫፻