Loading...
Language: Amharic
አንድ ሰው ከተሻሁድ በኋላ ይጸልያል -
اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ بِأَنَّ لَكَ الْحَمْدَ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ الْمَنَّانُ، بَدِيعُ السَّمَوَاتِ وَالْأَرْضِ يَا ذَا الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ، يَا حَيُّ يَا قَيُّوْمُ
አላሁመ ኢኒ አሰአሉከ ቢ-አነ ለከል-ሀምዱ፣ ላ ኢላሀ ኢላ አንተል-መናኑ በዲኡስ-ሰማዋቲ ወል-አርዲ፣ ያ ዘል-ጀላሊ ወል-ኢክራም! ያ ሀዩ ያ ቀዩም
አላህ ሆይ፣ እጠይቅሃለሁ፣ ምስጋና ለአንተ ይገባልና፤ ከአንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ጸጋን እና ደግነትን ለጋሽ፣ የሰማያት እና የምድር ፈጣሪ፣ የክብር እና የልዕልና ጌታ ሆይ፣ ህያው የሆንክ ሆይ፣ ራስህን የቻልክ ሆይ። ከዚያም ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- «ምን ብሎ እንደጸለየ (ዱዓ እንዳደረገ) ታውቃላችሁን?» እነርሱም፡- «አላህ እና መልእክተኛው ያውቃሉ» አሉ። እሳቸውም እንዲህ አሉ፡- «ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ፣ አላህን በታላቁ ስሙ ጠርቶታል፤ በዚህ (ስም) በተጠራ ጊዜ ይመልሳል፤ በዚህም ሲጠየቅ ይሰጣል።»
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። ነሳኢ፡ ፲፫፻