Loading...
Language: Amharic
ነቢዩ ሙሀመድ (ሶ.ዐ.ወ) ጌታቸውን በዚህ አጠቃላይ እና ድንቅ ዱዓ ይለምኑ ነበር፦
اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ خَيْرَ الْمَسْأَلَةِ، وَخَيْرَ الدُّعَاءِ، وَخَيْرَ النَّجَاحِ، وَخَيْرَ الْعَمَلِ، وَخَيْرَ الثَّوَابِ، وَخَيْرَ الْحَيَاةِ، وَخَيْرَ الْمَمَاتِ، وَثَبِّتْنِيْ، وَثَقِّل مَوَازِينِيْ، وَحَقِّقْ إِيْمَانِيْ، وَارْفَعْ دَرَجَاتِيْ، وَتَقَبَّلْ صَلَاتِيْ، وَاغْفِرْ خَطِيْئَتِيْ، وَأَسْأَلُكَ الدَّرَجَاتِ الْعُلَى مِنَ الْجَنَّةِ، اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ فَوَاتِحَ الْخَيْرِ، وَخَوَاتِمَهُ، وَجَوَامِعَهُ، وَأَوَّلَهُ، وَآخِرَهُ وَظَاهِرَهُ، وَبَاطِنَهُ، وَالدَّرَجَاتِ الْعُلَى مِنَ الْجَنَّةِ آمِينْ، اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ خَيْرَ مَا آتِيْ، وَخَيْرَ مَا أَفْعَلُ، وَخَيْرَ مَا أَعْمَلُ، وَخَيْرَ مَا بَطَنَ، وَخَيْرَ مَا ظَهَرَ، وَالدَّرَجَاتِ الْعُلَى مِنَ الْجَنَّةِ آمِينْ، اَللَّهُمَّ إنِّي أَسْأَلُكَ أَنْ تَرْفَعَ ذِكْرِيْ، وَتَضَعَ وِزْرِيْ، وَتُصْلِحَ أَمْرِيْ، وَتُطَهِّرَ قَلْبِيْ، وَتُحَصِّنَ فَرْجِيْ، وَتُنَوِّرَ قَلْبِيْ، وَتَغْفِرَ لِي ذَنْۢبِيْ، وَأَسْأَلُكَ الدَّرَجَاتِ الْعُلَى مِنَ الْجَنَّةِ آمِينْ، اَللَّهُمَّ إنِّي أَسْأَلُكَ أَنْ تُبَارِكَ لِي فِي نَفْسِيْ، وَفِي سَمْعِيْ، وَفِي بَصَرِيْ، وَفِي رُوحِيْ، وَفِي خَلْقِيْ، وَفِي خُلُقِيْ، وَفِي أَهْلِيْ، وَفِي مَحْيَايَ، وَفِي مَمَاتِيْ، وَفِي عَمَلِيْ، فَتَقَبَّلْ حَسَنَاتِيْ، وَأَسْأَلُكَ الدَّرَجَاتِ الْعُلَى مِنَ الْجَنَّةِ، آمِينْ
አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከ ኸይረል መስአለቲ፣ ወኸይረድ ዱዓኢ፣ ወኸይረን ነጃሂ፣ ወኸይረል አ መሊ፣ ወኸይረስ ሰዋቢ፣ ወኸይረል ሀያቲ፣ ወኸይረል መማቲ። ወሰብቢትኒ፣ ወሰቅቂል መዋዚኒ፣ ወሀቅቂቅ ኢማኒ፣ ወርፈእ ደረጋቲ፣ ወተቀብበል ሶላቲ፣ ወግፊር ኸጢአቲ፣ ወአስአሉከድ ደረጋቲል ዑላ ሚነል ጀንነቲ (አሚን)። አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከ ፈዋቲሀል ኸይሪ፣ ወኸዋቲመሁ፣ ወጀዋሚአሁ፣ ወአውወለሁ ወአኺረሁ፣ ወዛሂረሁ ወባጢነሁ፣ ወድደረጋቲል ዑላ ሚነል ጀንነቲ (አሚን)...
«አላህ ሆይ! እኔ ምርጥ ጥያቄን፣ ምርጥ ዱዓን፣ ምርጥ ስኬትን፣ ምርጥ ስራን፣ ምርጥ ምንዳን፣ ምርጥ ህይወትን እና ምርጥ አሟሟትን እጠይቅሃለሁ። አጽናኝ፣ ሚዛኔንም (በመልካም ስራ) አክብድልኝ፣ እምነቴን አረጋግጥልኝ፣ ደረጃዬን ከፍ አድርግልኝ፣ ሶላቴን ተቀበለኝ፣ ስህተቴን ማርልኝ። ከጀነትም ከፍተኛውን ደረጃ እጠይቅሃለሁ (አሚን)። አላህ ሆይ! የመልካም ነገር መጀመሪያውን እና መጨረሻውን፣ ሁሉንም (ስብስቡን)፣ የፊተኛውን እና የኋለኛውን፣ ግልጹን እና ድብቁን፣ ከጀነትም ከፍተኛውን ደረጃ እጠይቅሃለሁ (አሚን)። አላህ ሆይ! የሚመጣውን ምርጥ ነገር፣ የምሰራውን ምርጥ ነገር፣ የድብቁን መልካም እና የግልጹን መልካም፣ ከጀነትም ከፍተኛውን ደረጃ እጠይቅሃለሁ (አሚን)።» (አል-ሀኪም፡ 1/520)
Reference: ሰሂህ (ሀይሰሚ)። መጅመዑዝ-ዘዋኢድ፡ ፲/፻፰