Loading...
Language: Amharic
አነስ (ረ.ዐ) እንደተናገሩት ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፡- «ከተውሂድ ሰዎች ጋር ተቀምጬ ታላቁን አላህን ከጠዋት (ፈጅር) ሶላት ጀምሮ ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ ማውሳቴ (ማስታወሴ)፣ ከኢስማኢል ልጆች አራት ባሮችን ነፃ ከማውጣት ይበልጥ ወደ እኔ የተወደደ ነው። እንዲሁም ከሰአት (አስር) ሶላት ጀምሮ ፀሀይ እስክትጠልቅ ድረስ አላህን ከሚያስታውሱ ሰዎች ጋር መቀመጤ፣ ከኢስማኢል ልጆች አራት ባሮችን ነፃ ከማውጣት ይበልጥ ወደ እኔ የተወደደ ነው።»
Reference: ሐሰን (አልባኒ)። አቡ ዳውድ፡ ፴፮፻፷፯