Loading...
Language: Amharic
አላህ በተከበረው ቁርአን እንዲህ ይላል፦
إِذْ تَسْتَغِيثُونَ رَبَّكُمْ فَاسْتَجَابَ لَكُمْ أَنِّي مُمِدُّكُم بِأَلْفٍ مِّنَ الْمَلَائِكَةِ مُرْدِفِينَ ﴿٩﴾ وَمَا جَعَلَهُ اللَّـهُ إِلَّا بُشْرَىٰ وَلِتَطْمَئِنَّ بِهِ قُلُوبُكُمْ ۚ وَمَا النَّصْرُ إِلَّا مِنْ عِندِ اللَّـهِ ۚ إِنَّ اللَّـهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ ﴿١٠﴾
ኢዝ ተስተጊሱነ ረበኩም ፈስተጃበ ለኩም አንኒ ሙሚዱኩም ቢአልፊም ሚነል መላኢከቲ ሙርዲፊን። ወማ ጀዐለሁላሁ ኢላ ቡሽራ ወሊተጥመኢንነ ቢሂ ቁሉቡኩም፤ ወመ ንነስሩ ኢላ ሚን ዒንዲላህ፤ ኢንነላሀ ዐዚዙን ሀኪም።
«(አስታውሱ) ጌታችሁን እርዳታ በጠየቃችሁ ጊዜ (ለእናንተ) የተቀበለላችሁና «እኔ በሺህ መላእክት ተከታታዮች ሲኾኑ እረዳችኋለሁ» (ያላችሁን ጊዜ)። አላህም (ድሉን) ብስራትና በእርሱም ልቦቻችሁ እንዲረጋጉበት እንጂ ለሌላ አላደረገውም። ድልም ከአላህ ዘንድ እንጂ ከሌላ አይደለም። አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና።» (ሱረቱል አንፋል፡ 9-10)
Reference: ሱራ አል-አንፋል ፰: ፱-፲