Loading...
Language: Amharic
وَلَقَدْ نَصَرَكُمُ اللَّـهُ بِبَدْرٍ وَأَنتُمْ أَذِلَّةٌ ۖ فَاتَّقُوا اللَّـهَ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ ﴿١٢٣﴾ إِذْ تَقُولُ لِلْمُؤْمِنِينَ أَلَن يَكْفِيَكُمْ أَن يُمِدَّكُمْ رَبُّكُم بِثَلَاثَةِ آلَافٍ مِّنَ الْمَلَائِكَةِ مُنزَلِينَ ﴿١٢٤﴾ بَلَىٰ ۚ إِن تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا وَيَأْتُوكُم مِّن فَوْرِهِمْ هَـٰذَا يُمْدِدْكُمْ رَبُّكُم بِخَمْسَةِ آلَافٍ مِّنَ الْمَلَائِكَةِ مُسَوِّمِينَ ﴿١٢٥﴾ وَمَا جَعَلَهُ اللَّـهُ إِلَّا بُشْرَىٰ لَكُمْ وَلِتَطْمَئِنَّ قُلُوبُكُم بِهِ ۗ وَمَا النَّصْرُ إِلَّا مِنْ عِندِ اللَّـهِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ ﴿١٢٦﴾
ወለቀድ ነሰረኩሙላሁ ቢበድሪን ወአንቱም አዚለሁ፤ ፈተቁላሀ ለዐለኩም ተሽኩሩን። ኢዝ ተቁሉ ሊል ሙእሚኒነ አለን የክፊየኩም አዩሚደኩም ረቡኩም ቢሰላሰቲ አላፊም ሚነል መላኢከቲ ሙንዘሊን። በላ፤ ኢን ተስቢሩ ወተተቁ ወየእቱኩም ሚን ፈውሪሂም ሀዛ ዩምዲድኩም ረቡኩም ቢኸምሰቲ አላፊም ሚነል መላኢከቲ ሙሰዊሚን። ወማ ጀዐለሁላሁ ኢላ ቡሽራ ለኩም ወሊተጥመኢንነ ቁሉቡኩም ቢህ፤ ወመ ንነስሩ ኢላ ሚን ዒንዲላሂል ዐዚዚል ሀኪም።
«በበድርም (ጦርነት) እናንተ ሒሳቦች (ደካሞች) ሳላችሁ አላህ በእርግጥ ረዳችሁ። አላህንም ፍሩ ታመሰግኑ ዘንድ። ለምእመናን፡- «ጌታችሁ በሶስት ሺህ መላእክት የተወረዱ ሲኾኑ ሊረዳችሁ አይበቃችሁምን» በምትል ጊዜ (አስታውስ)። አይደለም (ይበቃችኋል)፤ ብትታገሱና ብትጠነቀቁ፣ (ጠላቶቻችሁም) በዚህ ፍጥነታቸው ቢመጡባችሁ ጌታችሁ በአምስት ሺህ ሙሰወሚን (ምልክት የተደረገላቸው) መላእክት ይረዳችኋል። አላህም (ይህንን እርዳታ) ለእናንተ ብስራት ሊኾንና ልቦቻችሁም በእርሱ ሊረጋጉ እንጂ ለሌላ አላደረገውም። ድልም አሸናፊ ጥበበኛ ከኾነው አላህ ዘንድ እንጂ ከሌላ አይደለም።» (ሱረቱ ኣሊ-ኢምራን፡ 123-126)
Reference: ሱራ አሊ ኢምራን ፫: ፻፳፫-፻፳፮