Loading...
Language: Amharic
اَللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوْذُ بِكَ مِنَ الْعَجْزِ وَالْكَسَلِ وَالْجُبْنِ وَالْبُخْلِ وَالْهَرَمِ وَالْقَسْوَةِ وَالْغَفْلَةِ وَالْعَيْلَةِ وَالذِّلَّةِ وَالْمَسْكَنَةِ وَأَعُوْذُ بِكَ مِنَ الْفَقْرِ وَالْكُفْرِ وَالْفُسُوْقِ وَالشِّقَّاقِ وَالنِّفَقِ وَالسُّمْعَةِ والرِّيَاءِ وَأَعُوْذُ بِكَ مِنَ الصَّمَمِ وَالْبَكَمِ وَالْجُنُوْنِ وَالْجُذَامِ وَالْبَرَصِ وَسَيِّءِ الْأَسْقَامِ
አልላሁምመ ኢንኒ አኡዙ ቢከ ሚነል አጅዚ፣ ወል-ከሰሊ፣ ወል-ጁብኒ፣ ወል-ቡኽሊ፣ ወል-ሀረሚ፣ ወል-ቀስወቲ፣ ወል-ገፍለቲ፣ ወል-አይለቲ፣ ወዝ-ዚልለቲ፣ ወል-መስከነቲ። ወአኡዙ ቢከ ሚነል ፈቅሪ፣ ወል-ኩፍሪ፣ ወል-ፉሱቂ፣ ወሽ-ሺቃቂ፣ ወን-ኒፋቂ፣ ወስ-ሱምአቲ፣ ወር-ሪያኢ። ወአኡዙ ቢከ ሚነስ-ሰመሚ፣ ወል-በከሚ፣ ወል-ጁኑኒ፣ ወል-ጁዛሚ፣ ወል-በረሲ፣ ወሰይዪኢል አስቃም
«አላህ ሆይ! ከአቅም ማነስ፣ ከስንፍና፣ ከፍርሃት፣ ከስስት፣ ከእርጅና (ከመጃጀት)፣ ከልብ ድርቀት፣ ከቸልተኝነት፣ ከድህነት፣ ከውርደት እና ከምስኪንነት (ከችግር) በአንተ እጠበቃለሁ። እንዲሁም ከድህነት፣ ከክህደት፣ ከአመጽ፣ ከጭቅጭቅ (ከመለያየት)፣ ከኒፋቅ (ግብዝነት)፣ ከዝና እና ከይዩልኝ ባይነት በአንተ እጠበቃለሁ። እንዲሁም ከደንቆሮነት፣ ከዲዳነት፣ ከእብደት፣ ከሥጋ ደዌ፣ ከለምጽ እና ከመጥፎ በሽታዎች በአንተ እጠበቃለሁ።» (ሃኪም፡ 1/530)
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። ሰሂሑል ጃሚዕ፡ ፲፪፻፹፭