Loading...
Language: Amharic
በነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ላይ 10 ጊዜ ሰላቫት ማውረድ -
اَللَّھُمَّ صَلِّ عَلَی مُحَمَّدٍ وَّعَلَی آلِ مُحَمَّدٍ کَمَا صَلَّیْتَ عَلَی اِبْرَاھِیْمَ وَعَلَی آلِ اِبْرَاھِیْمَ اِنَّكَ حَمِیْدٌ مَّجِیْدٌ، اَللَّھُمَّ بَارِكْ عَلَی مُحَمَّدٍ وَّعَلَی آلِ مُحَمَّدٍ کَمَا بَارَکْتَ عَلَی اِبْرَاھِیْمَ وَعَلَی آلِ اِبْرَاھِیْمَ اِنَّكَ حَمِیْدٌ مَّجِیْدٌ
አላሁመ ሰሊ አላ ሙሀመዲን ወ አላ አሊ ሙሀመዲን፣ ከማ ሰለይታ አላ ኢብራሂመ ወ አላ አሊ ኢብራሂመ፣ ኢነከ ሀሚዱን መጂድ። አላሁመ ባሪክ አላ ሙሀመዲን ወ አላ አሊ ሙሀመዲን፣ ከማ ባረክተ አላ ኢብራሂመ ወ አላ አሊ ኢብራሂመ፣ ኢነከ ሀሚዱን መጂድ።
አላህ ሆይ፣ በኢብራሂም እና በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እዝነትህን እንዳወረድክ፣ በሙሀመድ (ሶ.ዐ.ወ) እና በሙሀመድ (ሶ.ዐ.ወ) ቤተሰብ ላይ እዝነትህን አውርድ። አንተ ምስጉን እና ታላቅ ነህና። አላህ ሆይ፣ በኢብራሂም እና በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ በረከትህን እንዳወረድክ፣ በሙሀመድ እና በሙሀመድ ቤተሰብ ላይ በረከትህን አውርድ። አንተ ምስጉን እና ታላቅ ነህና። ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «በጠዋት 10 ጊዜ እና በማታ 10 ጊዜ በእኔ ላይ ሰላቫት ያወረደ ሰው፣ የፍርድ ቀን (ያውመል ቂያማ) የእኔን አማላጅነት ያገኛል።»
Reference: አጥ-ጠበራኒ፣ ሰሂህ አት-ተርጊብ ወ አት-ተርሂብ ፩/፪፻፸፫