Loading...
Language: Amharic
ሶስት ጊዜ ይበሉ፡
بِسْمِ اللَّهِ الَّذِيْ لَا يَضُرُّ مَعَ اسْمِهِ شَيْءٌ فِي الْأَرْضِ وَلَا فِي السَّمَاءِ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
ቢስሚላሂለዚ ላ የዱሩ መአስሚሂ ሸይኡን ፊል-አርዲ ወ ላ ፊስ-ሰማኢ ወ ሁወስ-ሰሚዑል-አሊም።
በአላህ ስም፣ በስሙ (አማካኝነት) በምድርም ሆነ በሰማይ ውስጥ ምንም ነገር ሊጎዳ በማይችለው፤ እርሱ ሰሚ እና አዋቂ ነው። ኡስማን (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡- ማንም ሰው ሶስት ጊዜ፡- «በአላህ ስም፣ በስሙ (አማካኝነት) በምድርም ሆነ በሰማይ ውስጥ ምንም ነገር ሊጎዳ በማይችለው፤ እርሱ ሰሚ እና አዋቂ ነው» ያለ፣ እስከ ጠዋት ድረስ ድንገተኛ መከራ አይደርስበትም፤ ይህንን በጠዋት ያለ ሰው፣ እስከ ማታ ድረስ ድንገተኛ መከራ አይደርስበትም።
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። አቡ ዳውድ፡ ፶፻፹፰