Loading...
Language: Amharic
ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ይህን ዱዓ ያደርጉ ነበር፦
اَللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي خَطِيْئَتِيْ وَجَهْلِيْ وَإِسْرَافِي فِي أَمْرِيْ وَمَا أَنْتَ أَعْلَمُ بِهِ مِنِّي اَللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي جِدِّيْ وَهَزَلِيْ وَخَطَئِيْ وَعَمْدِيْ وَكُلُّ ذَلِكَ عِنْدِيْ اَللَّهُمَ اغْفِرْ لِي مَا قَدَّمْتُ وَمَا أَخَّرْتُ وَمَا أَسْرَرْتُ وَمَا أَعْلَنْتُ وَمَا أَنْتَ أَعْلَمُ بِهِ مِنِّي أَنْتَ الْمُقَدِّمُ وَأَنْتَ الْمُؤَخِّرُ وَأَنْتَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرٌ
አልላሁምመግፊር ሊ ኸጢአቲ ወጀህሊ ወኢስራፊ ፊ አምሪ ወማ አንተ አዕለሙ ቢሂ ሚንኒ። አልላሁምመግፊር ሊ ጂድዲ ወሀዝሊ ወኸጠኢ ወአምዲ ወኩልሉ ዛሊከ ኢንዲ። አልላሁምመግፊር ሊ ማ ቀድደምቱ ወማ አኽኸርቱ ወማ አስረርቱ ወማ አዕለንቱ ወማ አንተ አዕለሙ ቢሂ ሚንኒ። አንተል ሙቀድዲሙ ወአንተል ሙአኽኺሩ ወአንተ አላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር
«አላህ ሆይ! ስህተቴን፣ አለማወቄን፣ በነገሬ ላይ ድንበር ማለፌንና አንተ ከኔ ይበልጥ የምታውቀውን (ወንጀል) ሁሉ ማርልኝ። አላህ ሆይ! ስሜታዊነትና መጫወት፣ ስህተትና ሆን ብሎ ማጥፋት፣ ይህ ሁሉ እኔ ዘንድ አለና ማርልኝ። አላህ ሆይ! ያስቀደምኩትንና ያቆየሁትን፣ የደበቅኩትንና የገለፅኩትን፣ አንተ ከኔ በበለጠ የምታውቀውን ሁሉ ማርልኝ። ፊተኛውም አንተ ነህ፣ ኋለኛውም አንተ ነህ። አንተም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህ።»
Reference: ሙስሊም፡ ፪፯፩፱