Loading...
Language: Amharic
ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ጠዋትና ማታ የሚሉት በጣም አስፈላጊ ዱዓ፦
اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي دِينِيْ وَدُنْيَايَ وَأَهْلِيْ، وَمَالِيْ، اَللَّهُمَّ اسْتُرْ عَوْرَاتِيْ، وَآمِنْ رَوْعَاتِيْ، اَللَّهُمَّ احْفَظْنِي مِنْ بَيْنِ يَدَيَّ وَمِنْ خَلْفِي وَعَنْ يَمِيْنِيْ وَعَنْ شِمَالِي وَمِنْ فَوْقِيْ وَأَعُوْذُ بِعَظَمَتِكَ أَنْ أُغْتَالَ مِنْ تَحْتِيْ
አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከል አፍወ ወል አፊየተ ፊድ ዱኒያ ወል አኼራህ። አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከል አፍወ ወል አፊየተ ፊ ዲኒ ወዱኒያየ ወአህሊ ወማሊ። አልላሁምመ ስቱር አውራቲ ወአሚን ረውአቲ። አልላሁምመህፈዝኒ ሚን በይኒ የደይየ ወሚን ኸልፊ ወአን የሚኒ ወአን ሺማሊ ወሚን ፈውቂ፣ ወአዑዙ ቢአዘመቲከ አን ኡግታለ ሚን ተህቲ
«አላህ ሆይ! እኔ በዱኒያም በአኼራም ይቅርታን እና ደህንነትን እጠይቅሃለሁ። አላህ ሆይ! እኔ በሃይማኖቴ፣ በዱኒያዬ፣ በቤተሰቤ እና በንብረቴ ይቅርታን እና ደህንነትን እጠይቅሃለሁ። አላህ ሆይ! ነውሬን ሸፍንልኝ፣ ፍራቻዬንም አረጋጋልኝ። አላህ ሆይ! ከፊቴ፣ ከኋላዬ፣ በቀኜ፣ በግራዬ፣ ከላዬም ጠብቀኝ። ከሥሬ በመወሰድ (መሬት ተሰንጥቃ በመዋጥ) ባንተ ታላቅነት እጠበቃለሁ።»
Reference: ሷሒሕ። አቡ ዳውድ፡ ፭፸፸፬