Loading...
Language: Amharic
አል-ሀሰን ኢብን አሊ (ረ.ዐ) እንደተረኩት፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) በዊትር ወቅት የምላቸውን አንዳንድ ቃላት አስተማሩኝ -
اَللَّهُمَّ اهْدِنِيْ فِيمَنْ هَدَيْتَ وَعَافِنِي فِيمَنْ عَافَيْتَ وَتَوَلَّنِيْ فِيمَنْ تَوَلَّيْتَ وَبَارِكْ لِي فِيمَا أَعْطَيْتَ وَقِنِي شَرَّ مَا قَضَيْتَ فَإِنَّكَ تَقْضِي وَلَا يُقْضَى عَلَيْكَ إِنَّهُ لَا يَذِلُّ مَنْ وَالَيْتَ وَلَا يَعِزُّ مَنْ عَادَيْتَ تَبَارَكْتَ رَبَّنَا وَتَعَالَيْتَ
አላሁመ-ህዲኒ ፊመን ሀደይተ፣ ወ ዐፊኒ ፊመን ዐፈይተ፣ ወ ተወለኒ ፊመን ተወለይተ፣ ወ ባሪክ ሊ ፊማ አ'ጠይተ፣ ወ ቂኒ ሸረ ማ ቀደይተ፣ ፈኢነከ ተቅዲ ወ ላ ዩቅዳ 'አለይከ፣ ኢነሁ ላ የዚሉ መን ዋለይተ፣ ወ ላ የ 'ኢዙ መን 'አደይተ፣ ተባረክተ ረበና ወ ተአለይተ
አላህ ሆይ! ከመራሃቸው ሰዎች ጋር ምራኝ፣ ብርታት ከሰጠሃቸውም ሰዎች ጋር አበርታኝ። ከተንከባከብካቸው ሰዎች ጋር በእንክብካቤህ ያዘኝ። በሰጠኸኝ ነገር ባርክልኝ። ከወሰንከው ክፉ ነገር ጠብቀኝ። በእርግጥ አንተ ትወስናለህ እንጂ አይወሰንብህምና፤ አንተ የተንከባከብከው ሰው አይዋረድም፤ ጠላት ያደረግከውም ክብርን አይቀምስም። ጌታችን ሆይ የተባረክ እና የተላቅክ ነህ።
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። አቡ ዳውድ፡ ፲፬፻፳፭